Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 14:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እን​ዳ​ል​ሃ​ቸው፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ብዛት የእ​ነ​ዚ​ህን ሕዝብ ኀጢ​አት ይቅር በል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው ሁሉ እንደ ፍቅርህ ታላቅነት መጠን እባክህ አሁንም የዚህን ሕዝብ ኀጢአት ይቅር በል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ይህን ሕዝብ ከግብጽ ምድር ካወጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እንዳልከው፥ እባክህ፥ እንደ ጽኑ ፍቅርህ ብዛት የዚህን ሕዝብ በደል ይቅር በል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አሁንም ጌታ ሆይ፤ ታላቅ በሆነውና በማይለወጠው ፍቅርህ ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ ምሕረት እንዳደረግህላቸው የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ይህን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ካወጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው፥ እባክህ፥ እንደ ምሕረትህ ብዛት የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 14:19
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ህም ቤት ቢጸ​ል​ዩና ቢለ​ም​ኑህ፥ አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ምድር መል​ሳ​ቸው።


እኔ የዋህ ነኝና ነፍ​ሴን ጠብ​ቃት፤ አም​ላኬ ሆይ፥ አን​ተን የታ​መ​ነ​ውን ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው።


አሁ​ንም ይህን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ትላ​ቸው እን​ደ​ሆነ ይቅር በላ​ቸው፤ ያለ​ዚያ ግን ከጻ​ፍ​ኸው መጽ​ሐፍ ደም​ስ​ሰኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያል​ኸ​ኝን ነገር አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ በፊቴ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተ​ሀ​ልና ከሁሉ ይልቅ ዐው​ቄ​ሃ​ለ​ሁና”አለው።


“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


የም​ድ​ሩ​ንም ሣር በልቶ ይጨ​ር​ሳል፤ እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይቅር እን​ድ​ትል እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እን​ድ​ት​ተው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።


እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።


የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል፤ ጌታም ያስነሣዋል፤ ኀጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች