Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በል​ቤም አሰ​ብሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ “ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወለድ ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ” ብዬ ተጣ​ላ​ኋ​ቸው፤ ትል​ቅም ጉባኤ ሰበ​ሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ነገሩን በሐሳቤ ካወጣሁ ካወረድሁ በኋላ፣ መኳንንቱንና ሹማምቱን ገሠጽኋቸው፤ “ከገዛ አገራችሁ ሰዎች ላይ እንዴት ዐራጣ ትበላላችሁ” አልኋቸውም። ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለመነጋገር ታላቅ ስብሰባ ጠራሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በልቤም አሰብሁና መኳንንቶቹንና ሹማምቱን ተከራከርኋቸው፥ እንዲህም አልኋቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁ በአራጣ ታበድራላችሁ”፤ ትልቅ ጉባኤም ሰበሰብሁባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ላደርገው የሚገባኝንም በልቤ ወስኜ የሕዝቡ መሪዎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች “እናንተ እኮ የገዛ ወንድሞቻችሁን በመጨቈን አራጣ ታስከፍላላችሁ!” በማለት በቊጣ ገሠጽኳቸው። ለችግሩም መፍትሔ ለማግኘት ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቤ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በልቤም አሰብሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም፦ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ ብዬ ተጣላኋቸው፥ ትልቅም ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 5:7
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና ጠብ​ቀኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ኀይ​ላ​ቸው ነው፥ ለመ​ሲሑ የመ​ድ​ኀ​ኒቱ መታ​መኛ ነው።


ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።


ቍጣ​ዬም ይጸ​ና​ባ​ች​ኋል፤ በሰ​ይ​ፍም አስ​ገ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም መበ​ለ​ቶች፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ድሀ-አደ​ጎች ይሆ​ናሉ።


“ከአ​ንተ ጋር ለተ​ቀ​መ​ጠው ለድ​ሃው ወገ​ንህ ብር ብታ​በ​ድ​ረው፥ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ አራ​ጣም አታ​ስ​ከ​ፍ​ለው።


በአ​ንቺ ውስጥ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ተቀ​በሉ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ጣና ትርፍ ወስ​ደ​ዋል፤ ቀማ​ኛ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ፈጸ​ምሽ፤ እኔ​ንም ረሳ​ሽኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች ሆይ! ይብ​ቃ​ችሁ፤ ግፍ​ንና ዐመ​ፅን አስ​ወ​ግዱ፤ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ፤ ቅሚ​ያ​ች​ሁን ከሕ​ዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።


ወን​ድ​ምህ ከአ​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእ​ርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አት​ው​ሰድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።


ስለ​ዚህ ከአ​ሁን ጀምሮ በሥጋ የም​ና​ው​ቀው የለም፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በሥጋ ብና​ው​ቀው አሁን ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የም​ና​ው​ቀው አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን ኬፋ ወደ አን​ጾ​ኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃ​ወ​ም​ሁት፤ ነቅ​ፈ​ውት ነበ​ርና።


ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኀጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጻቸው።


ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች