Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኑን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጣቸውን ድርሻ ሠሩ። የበራክያ ልጅ መሹላምም በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት በኩል ያለውን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከእርሱ በኋላ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በጓዳው አንጻር ያለውን አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:30
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዕቃ ቤቶ​ችም ላይ ካህ​ኑን ሰሌ​ም​ያን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳዶ​ቅን፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም ፈዳ​ያን ሾምሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የመ​ታ​ንያ ልጅ የዘ​ኩር ልጅ ሐናን ነበረ፤ እነ​ር​ሱም የታ​መኑ ሆነው ተገኙ፤ ሥራ​ቸ​ውም ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ማከ​ፋ​ፈል ነበረ።


ከዚ​ያም በኋላ የሄ​ሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የም​ሥ​ራቁ በር ጠባቂ የሴ​ኬ​ንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ራፊ ልጅ መል​ክያ እስከ ናታ​ኒ​ምና እስከ ነጋ​ዴ​ዎቹ ቤት ድረስ በሐ​ሜ​ፍ​ቃድ በር አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ማዕ​ዘኑ መውጫ ድረስ ሠራ።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።


ጦብያ የአ​ራሄ ልጅ የሴ​ኬ​ንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐ​ናን የቤ​ራ​ክ​ያን ልጅ የሜ​ሱ​ላ​ምን ሴት ልጅ ስላ​ገባ፥ በይ​ሁዳ ብዙ ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ተማ​ም​ለው ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች