Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኑን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጣቸውን ድርሻ ሠሩ። የበራክያ ልጅ መሹላምም በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት በኩል ያለውን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ሎ​ምያ ልጅ ሐና​ን​ያና የሴ​ሌፍ ስድ​ስ​ተ​ኛው ልጁ ሐኖን ሌላ​ውን ክፍል ሠሩ። ከዚ​ያም በኋላ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም በሙ​ዳየ ምጽ​ዋቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከእርሱ በኋላ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በጓዳው አንጻር ያለውን አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:30
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዕቃ ቤቶችም ላይ ካህኑን ሰሌምያን፥ ጸሐፊውንም ሳዶቅን፥ ከሌዋውያኑም ፈዳያን ሾምሁ፥ ከእነርሱም ጋር የማታንያ ልጅ የዘኩር ልጅ ሐናን ነበረ፥ እነርሱም የታመኑ ሆነው ተገኙ፥ ሥራቸውም ለወንድሞቻቸው ማከፋፈል ነበረ።


ከዚያ በኋላ የኢሜር ልጅ ጻዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። ከእርሱም በኋላ “የምሥራቅ በር” ጠባቂ የሆነው የሼካኔያ ልጅ ሼማዔያ አደሰ።


ከእርሱም በኋላ የወርቅ አንጥረኛው ልጅ ማልኪያ ከ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ቤት፥ የነጋዴዎቹ ቤት ጀምሮ እስከ “የመሰብሰቢያ በር” ፊት ለፊት ያለውንና እስከ ማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ድረስ አደሰ።


በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።


በይሁዳ ለእርሱ የማሉለት ብዙ ሰዎች ነበሩና፤ የአራሕ ልጅ የሼካንያ አማች ነበረና፥ ልጁ ይሆሐናንም የቤራክያን ልጅ የሜሹላምን ሴት ልጅ አግብቷልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች