Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 10:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እኛም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ሕዝ​ቡም፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችን ቤቶች በተ​ወ​ሰነ ጊዜ በየ​ዓ​መቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት አም​ጥ​ተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይቃ​ጠል ዘንድ ስለ ዕን​ጨት ቍር​ባን ዕጣ ተጣ​ጣ​ልን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 “እኛ፣ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በሕጉ እንደ ተጻፈው፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚነድደውን ዕንጨት የእያንዳንዳችን ቤተ ሰብ መቼ ወደ አምላካችን ቤት ማምጣት እንዳለበት ለመወሰን ዕጣ ተጣጣልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 10:34
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​ል​ዓ​ዛ​ርና ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች መካ​ከል የን​ዋ​ያተ ቅዱ​ሳ​ቱና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለ​ቆች ነበ​ሩና እነ​ዚ​ህና እነ​ዚያ እን​ዲህ በዕጣ ተመ​ደቡ።


መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ዕጣ ለኢ​ያ​ሬብ ወጣ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ለኢ​ያ​ድያ፥


ሰሎ​ሞ​ንም እን​ዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝ​ግባ እን​ጨት እንደ ላክ​ህ​ለት፥ እን​ዲሁ ለእኔ አድ​ርግ።


ከዚ​ያም በኋላ ዘወ​ትር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የመ​ባ​ቻ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ት​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ሁሉ መሥ​ዋ​ዕት፥ ሰውም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የሰ​ጠ​ውን ቍር​ባን አቀ​ረቡ።


የሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ፤ ከቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከዐ​ሥሩ ክፍል አንዱ በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዘጠ​ኙም በሌ​ሎች ከተ​ሞች ይቀ​መጡ ዘንድ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


በየ​ጊ​ዜ​ውም ዕን​ጨት ለሚ​ሸ​ከሙ ሰዎች ቍር​ባን፥ ለበ​ኵ​ራ​ቱም ሥር​ዐት አደ​ረ​ግሁ። “አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በመ​ል​ካም አስ​በኝ።”


ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።


ሊባ​ኖስ ለማ​ን​ደጃ እን​ስ​ሶ​ች​ዋም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አይ​በ​ቁም።


“የስ​ንዴ ዱቄት ወስ​ደህ ዐሥራ ሁለት ኅብ​ስት ጋግር፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ኅብ​ስት ውስጥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።


እነ​ዚ​ህ​ንም ስድ​ስት ስድ​ስ​ቱን በሁ​ለት ተርታ አድ​ር​ገህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በን​ጹሕ ገበታ ላይ አኑ​ራ​ቸው።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ ቍር​ባ​ኔን፥ መባ​ዬ​ንና የበጎ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ቴን በበ​ዓ​ላት ቀኖች ታቀ​ር​ቡ​ልኝ ዘንድ ጠብቁ።


ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች