Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል። በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል፤ በሃያኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሃያኛው ዓመት በኪስሌው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ እንዲህ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሐካልያ ልጅ ነህምያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሃያኛው ዓመት ኪስሌው ተብሎ በሚጠራው ወር እኔ ነህምያ ዋና ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ነበርኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሃያኛው ዓመት በካሴሉ ወር እንዲህ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 1:1
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦስት ቀንም ሳያ​ልፍ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ሰዎች ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ​ዚህ ነገ​ርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጡ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።


ያተ​ሙ​ትም እነ​ዚህ ናቸው፤ የሐ​ካ​ልያ ልጅ ሐቴ​ር​ሰታ ነህ​ምያ፥ ሴዴ​ቅ​ያስ፤


በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ንጉ​ሡም በይ​ሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘ​ዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከን​ጉሡ ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ከሃ​ያ​ኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወን​ድ​ሞች ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​በ​ላ​ንም።


በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች