Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከወ​ን​ድ​ሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይ​ሁዳ መጡ፤ እኔም የዳ​ኑ​ትን፥ ከም​ር​ኮም የተ​ረ​ፉ​ትን የአ​ይ​ሁ​ድን ነገር፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ነገር ጠየ​ቅ​ኋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከወንድሞቼ አንዱ የሆነው አናኒ፣ ከሌሎች ጥቂት ሰዎች ጋራ ከይሁዳ መጣ፤ እኔም ከምርኮ ስለ ተረፉት የአይሁድ ቅሬታዎችና ስለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከወንድሞቼ አንዱ ሐናኒ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከይሁዳ መጡ፥ እኔም ከምርኮ ስለተረፉት የአይሁድ ትሩፋንና ሰለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከወንድሞቼ አንዱ ሐናኒ ተብሎ የሚጠራው ሌሎች ሰዎችን አስከትሎ ከይሁዳ ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ስለ ኢየሩሳሌምና ወደ ባቢሎን ተማርከው ከመወሰድ ስለ ተረፉትና በሕይወት ስላሉት አይሁድ ሁኔታ ጠየቅኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ ከወንድሞቼ አንዱ አናኒ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን ከምርኮ የተረፉትን የአይሁድን ነገር የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 1:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወን​ድ​ሜን ሃና​ኒ​ንና የግ​ን​ቡን አለቃ ሐና​ን​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ሾም​ኋ​ቸው፤ እር​ሱም እው​ነ​ተኛ ከሌ​ሎ​ቹም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ነበረ።


በዚያ በተ​ማ​ረ​ኩ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከእ​ና​ንተ የዳ​ኑት ያስ​ቡ​ኛል፤ ለሰ​ሰ​ኑ​በት፥ ከእ​ኔም ለራ​ቁ​በት ለል​ቡ​ና​ቸው፥ ለሰ​ሰኑ፥ ጣዖ​ት​ንም ለተ​ከ​ተሉ ለዓ​ይ​ኖ​ቻ​ቸው ማልሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ እን​ዳ​መ​ለኩ መጠን ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ፊታ​ቸ​ውን ይነ​ጫሉ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


በዚያ ለመ​ቀ​መጥ በል​ባ​ቸው ተስፋ ወደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጓት ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለሱ ዘንድ በግ​ብፅ ለመ​ኖር ከመጡ ከይ​ሁዳ ቅሬታ ወገን የሚ​ያ​መ​ል​ጥና የሚ​ቀር፥ ወደ​ዚ​ያም የሚ​መ​ለስ አይ​ኖ​ርም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጥም በቀር ማንም አይ​መ​ለ​ስም።”


ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን።


ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ከሀ​ገሩ ድሆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች