Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሚክያስ 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ፣ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚክያስ 7:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀኝ እጁ ይጋ​ር​ድህ።


ይቅር ባይ ሰው ታላቅና ክቡር ነው፤ ነገር ግን የታመነ ሰው የሚገኘው በድካም ነው።


ወይራ በተ​መታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ቀር፥ አራት ወይም አም​ስት በዛ​ፊቱ ጫፍ እን​ደ​ሚ​ገኝ፥ በእ​ርሱ ዘንድ ቃር​ሚያ ይቀ​ራል” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህ ሁሉ በሀ​ገር ውስጥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይሆ​ናል። የወ​ይራ ፍሬ ለቀማ ባለቀ ጊዜ በቃ​ር​ሚ​ያው ውስጥ የወ​ይራ ፍሬ እን​ደ​ሚ​ለ​ቀም እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ይቃ​ር​ሟ​ቸ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ የጻ​ድ​ቁን ድንቅ ተስፋ ከም​ድር ዳርቻ ሰም​ተ​ናል። እነ​ርሱ ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለሚ​ያ​ፈ​ርሱ ወን​ጀ​ለ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” አሉ።


በረ​ዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረ​ገ​ፈች የክ​ብሩ ተስፋ አበባ አስ​ቀ​ድማ እን​ደ​ም​ት​በ​ስል በለስ ትሆ​ና​ለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይ​ቀ​በ​ላት ይበ​ላት ዘንድ ይፈ​ጥ​ናል።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


እናቴ ሆይ! ለም​ድር ሁሉ የክ​ር​ክ​ርና የጥል ሰው የሆ​ን​ሁ​ትን እኔን ወል​ደ​ሽ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! ለማ​ንም አል​ጠ​ቀ​ም​ሁም፤ ማንም እኔን አል​ጠ​ቀ​መ​ኝም፤ ከሚ​ረ​ግ​ሙ​ኝም የተ​ነሣ ኀይሌ አለቀ።


በአ​ን​ደ​ኛ​ዪቱ ቅር​ጫት አስ​ቀ​ድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚ​መ​ስል እጅግ መል​ካም በለስ ነበ​ረ​ባት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቅር​ጫት ከክ​ፋቱ የተ​ነሣ ይበላ ዘንድ የማ​ይ​ቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበ​ረ​ባት።


እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።


አንተ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ማሜ ላይ ኀዘ​ንን ጨም​ሮ​ብ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! በል​ቅ​ሶዬ ጩኸት ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም ብለ​ሃል።


“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​መ​ጡት በም​ድ​ራ​ቸው ያለው የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች