Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሚክያስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፤ ወደ ይሁዳ መጥቷል፥ ወደ ሕዝቤ በር ወደ ኢየሩሳሌምም ደርሶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሰማርያ ቊስል ሊፈወስ የሚችል አይደለም፤ ይህም ሥቃይ ወደ ይሁዳ ደርሶአል፤ ሕዝቤ ወደሚሰበሰቡበት ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይም ተዛምቶአል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሚክያስ 1:9
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በን​ጉሡ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰ​ዳ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ራፋ​ስ​ቂ​ስን ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላከው፤ እር​ሱም በአ​ጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኵሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆመ።


የሚ​ያ​ሳ​ዝ​ኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበ​ረ​ታሉ? ቍስ​ሌስ ስለ ምን የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆነ? ስለ ምንስ አል​ሽ​ርም አለ? እንደ ሐሰ​ተኛ ምንጭ፥ እን​ዳ​ል​ታ​መ​ነች ውኃም ሆነ​ብኝ።


ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል።


ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፥ ስለ ኃጢአትህም አፈረስሁህ።


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች