Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በመንገድ ዳርም አንድ የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ ሲሄድ ከቅጠል በቀር ምንም ስላላገኘባት፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ፍሬ አይኑርብሽ!” አላት፤ የበለሷም ዛፍ ወዲያውኑ ደረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በመንገድ ዳር የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠል በስተቀር ምንም አላገኘባትም፤ “እንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስዋ ዛፍም ወዲያውኑ ደረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አንዲት የበለስ ዛፍ በመንገድ ዳር አየና ወደ እርስዋ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። ስለዚህ “ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ!” አላት። ዛፊቱም ወዲያውኑ ደረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 21:19
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አጥር አጠ​ርሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቈፈ​ርሁ፤ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም ለቅሜ አወ​ጣሁ፤ ምርጥ የሆ​ነ​ው​ንም ወይን ተከ​ልሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግ​ሞም የመ​ጥ​መ​ቂያ ጕድ​ጓድ ማስ​ሁ​ለት፤ ወይ​ን​ንም ያፈራ ዘንድ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ዳሩ ግን እሾ​ህን አፈራ።


አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በወ​ይን ላይ ፍሬ፥ በበ​ለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠ​ልም ይረ​ግ​ፋል፤ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ አለ​ፈ​ባ​ቸ​ውም።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው “በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች?” ብለው ተደነቁ።


መልሶም “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፤” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።


ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።


እነሆ፥ ምሳር በዛ​ፎች ላይ ተቃ​ጥ​ቶ​አል፤ መል​ካም ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ወደ እሳ​ትም ይጥ​ሉ​ታል።”


በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል።


በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።


የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


ዐመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፤ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ፤” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች