Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 9:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47-48 ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጕለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጉለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ዐይንህም ቢያስትህ፥ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን እያለህ፥ ወደ ገሃነም ከምትጣል ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47-48 ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 9:47
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሴቲ​ቱም ዛፉ ለመ​ብ​ላት ያማረ እን​ደ​ሆነ፥ ለዐ​ይ​ንም ለማ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጐ​መጅ፥ መል​ካ​ም​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍ​ሬው ወሰ​ደ​ችና በላች፤ ለባ​ል​ዋም ደግሞ ሰጠ​ችው፤ እር​ሱም ከእ​ር​ስዋ ጋር በላ።


“ከዐ​ይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁም፤


ዐይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዐይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።


“ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም።


አሁ​ንስ ደስ ማሰ​ኘ​ታ​ችሁ ወዴት አለ? ቢቻ​ላ​ች​ሁስ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም እንኳ ቢሆን አው​ጥ​ታ​ችሁ ትሰ​ጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስ​ክ​ራ​ችሁ ነኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች