Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጲላጦስም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አላቸው። እነርሱ ግን “ስቀለው!” እያሉ ጩኸት አበዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው!” እያሉ የባሰ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጲላጦስም፥ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን፥ “ስቀለው” እያሉ የባሰ ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጲላጦስም “ለምን? ያደረገው በደል ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም “ስቀለው!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጲላጦስም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱ ግን፦ ስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 15:14
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ የሚ​ሹህ ሁሉ በአ​ንተ ሐሤት ያድ​ርጉ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወ​ድዱ፥ “ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


ክፉ​ዎ​ች​ንም ስለ መቃ​ብሩ፥ ባለ​ጸ​ጎ​ች​ንም ስለ ሞቱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ምና፥ ከአ​ፉም ሐሰት አል​ተ​ገ​ኘ​በ​ት​ምና።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።


“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


እነርሱም ዳግመኛ “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ።


ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።


እነ​ርሱ ግን፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ይጮሁ ነበር።


ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው።


በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።”


የመቶ አለ​ቃ​ውም የሆ​ነ​ውን ነገር አይቶ፥ “ይህ ሰው በእ​ው​ነት ጻድቅ ነበረ”ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው።


ጲላ​ጦ​ስም፥ “እው​ነት ምን​ድ​ነው?” አለው፤ ይህ​ንም ተና​ግሮ ዳግ​መኛ ወደ አይ​ሁድ ወጣና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አን​ዲት ስን​ኳን በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ራሳ​ችሁ ውሰ​ዱና ስቀ​ሉት፤ እኔስ በእ​ርሱ ላይ በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።


ለሞ​ትም የሚ​ያ​በቃ ምንም በደል ባላ​ገ​ኙ​በት ጊዜ እን​ዲ​ገ​ድ​ለው ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።


አይ​ሁ​ዳዊ እን​ደ​ሆ​ነም ባወቁ ጊዜ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአ​ንድ ድምፅ ጮሁ።


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች