Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባ​ለው ቦታ በደ​ረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀ​ሉት፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎች አን​ዱን በቀኙ አን​ዱ​ንም በግ​ራው ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ቀራንዮ የተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ሰቀሉት፤ ወንጀለኞቹንም አንዱን በቀኙ፣ ሌላውን በግራው ሰቀሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ቀራንዮ ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ እርሱን፥ ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኙ አንዱን በግራው በኩል ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ቀራንዮ ወይም የራስ ቅል ወደ ተባለ ስፍራም በደረሱ ጊዜ በዚያ ኢየሱስን ሰቀሉት፤ እንዲሁም ሁለቱን ወንጀለኞች በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:33
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።


ለደቀ መዛሙርቱ “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል፤” አለ።


የሰው ልጅ በኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ሰዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፤ ይሰ​ቅ​ሉ​ታል፤ ይገ​ድ​ሉ​ታል፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ሣል።” 10፥33-34፤ ሉቃ. 9፥22፤ 18፥31-33።


ይህም በምን ዐይ​ነት ሞት ይሞት ዘንድ እን​ዳ​ለው ሲያ​መ​ለ​ክት የተ​ና​ገ​ረው የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


ሙሴ በም​ድረ በዳ እባ​ቡን እንደ ሰቀ​ለው የሰው ልጅ እን​ዲሁ ይሰ​ቀል ዘንድ አለው።


ስለ እር​ሱም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ከመ​ስ​ቀል አው​ር​ደው በመ​ቃ​ብር ቀበ​ሩት።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ፥ እና​ንተ ክዳ​ችሁ በዕ​ን​ጨት ላይ ሰቅ​ላ​ችሁ የገ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሣው።


እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”


በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ረ​ገመ ነውና ሥጋው በእ​ን​ጨት ላይ አይ​ደር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር እን​ዳ​ታ​ረ​ክስ በእ​ር​ግጥ በዚ​ያው ቀን ቅበ​ረው።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች