Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ኢየሱስም፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። እነርሱም ልብሱን በዕጣ ተከፋፈሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ኢየሱስም “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፤” አለ። ልብሱንም ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፦ “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው!” አለ። ወታደሮቹም ዕጣ ተጣጥለው የኢየሱስን ልብስ ተከፋፈሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:34
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።”


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


ሰቀሉትም፤ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብት​ፈ​ቅ​ድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳ​ል​ፈው፤ ነገር ግን የአ​ንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይ​ሁን።”


እኔ ስለ እነ​ርሱ እለ​ም​ና​ለሁ፤ የም​ለ​ም​ንህ ስለ ዓለም አይ​ደ​ለም፤ ስለ ሰጠ​ኸኝ ነው እንጂ፤ ያንተ ናቸ​ውና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ጳው​ሎ​ስም፥ “በራ​ስህ ክፉ ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ሁላ​ች​ንም ከዚህ አለን” ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸ።


“አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አለ​ቆ​ቻ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረጉ ይህን ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አው​ቃ​ለሁ።


በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አት​ር​ገሙ።


የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።


በእ​ጃ​ችን ሥራ እያ​ገ​ለ​ገ​ልን እን​ደ​ክ​ማ​ለን፤ ይረ​ግ​ሙ​ናል፤ እኛ ግን እን​መ​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ ያሳ​ድ​ዱ​ናል፤ እኛ ግን እን​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ እን​ታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለ​ንም።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች