Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ያን የለ​መ​ኑ​ትን፥ ነፍስ በመ​ግ​ደ​ልና ሁከት በማ​ድ​ረግ የታ​ሰ​ረ​ው​ንም ሰው ፈታ​ላ​ቸው፤ ኢየ​ሱ​ስን ግን ለፈ​ቃ​ዳ​ቸው አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የሕዝብ ዐመፅ በማነሣሣትና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውን፣ እንዲፈታላቸውም የለመኑትን ያን ሰው ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንዳሻቸው እንዲያደርጉት አሳልፎ ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሁከት በመፍጠርና ሰውን በመግደል ምክንያት ታስሮ የነበረውን በጥያቄአቸው መሠረት አስፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንደ ፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ብጥብጥ በማስነሣትና ሰው በመግደል ታስሮ የነበረውን በርባንን በጥያቄአቸው መሠረት ለቀቀው፤ ኢየሱስን ግን እንደ ፍላጎታቸው አሳልፎ ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:25
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።


ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።


እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።”


ጲላ​ጦ​ስም የለ​መ​ኑት ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ ፈረ​ደ​በት።


በወ​ሰ​ዱ​ትም ጊዜ የቀ​ሬና ሰው ስም​ዖ​ንን ከዱር ሲመ​ለስ ያዙት፤ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱ​ስም በስ​ተ​ኋላ መስ​ቀ​ሉን አሸ​ከ​ሙት።


ሕዝ​ቡም፥ “ከገ​ሊላ ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ድረስ በመ​ላው ይሁዳ እያ​ስ​ተ​ማረ ሕዝ​ቡን ያው​ካል” እያሉ አጽ​ን​ተው ጮኹ።


ዳግ​መ​ኛም ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “በር​ባ​ንን እንጂ ይህን አይ​ደ​ለም፤” አሉ፤ በር​ባን ግን ወን​በዴ ነበር።


ከዚህ በኋላ ሊሰ​ቅ​ሉት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ተቀ​ብ​ለው ወሰ​ዱት።


እና​ንተ ግን ቅዱ​ሱ​ንና ጻድ​ቁን ካዳ​ች​ሁት፤ ነፍሰ ገዳ​ዩን ሰውም እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ላ​ችሁ ለመ​ና​ችሁ።


አሁ​ንም የመ​ረ​ጣ​ች​ሁ​ትን ንጉሥ እዩ፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ሰጣ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች