Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሙሴም አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን አቀ​ረበ፤ በው​ኃም አጠ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሙሴም አሮንንና ልጆቹን ወደ ፊት አወጣቸው፤ በውሃም ዐጠባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሙሴም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቅርቦ በውሃ አጠባቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 8:6
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።


ልብህ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽን​ገ​ላን አደ​ረ​ግህ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በው​ኃም ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል።


ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ሳት መሥ​ዋ​ዕት ያቃ​ጥሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሊያ​ገ​ለ​ግሉ በቀ​ረቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል።


አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አቅ​ር​በህ በውኃ ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።


ታጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ የሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁን ክፋት ከዐ​ይ​ኖች ፊት አስ​ወ​ግዱ፤ ክፉ ማድ​ረ​ግ​ንም ተዉ፤


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው።


ሙሴም ማኅ​በ​ሩን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታደ​ርጉ ዘንድ ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው” አላ​ቸው።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እን​ዲህ ስት​ሆኑ እነ​ማን ናችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም መን​ፈስ ታጥ​ባ​ች​ኋል፤ ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ጸድ​ቃ​ች​ኋ​ልም።


በውኃ ጥም​ቀ​ትና በቃሉ ይቀ​ድ​ሳ​ትና ያነ​ጻት ዘንድ፥


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች