Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን፥ ልብ​ሱ​ንም፥ የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን፥ ሁለ​ቱ​ንም አውራ በጎች፥ የቂ​ጣ​ው​ንም እን​ጀራ መሶብ ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም የክህነት ልብሱን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበውን ኰርማ ሁለቱን የበግ አውራዎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ ያለበትን መሶብ፥ አብረህ አምጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ ሌማት ውሰድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 8:2
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


ለአ​ሮ​ንም ልጆች የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ችን፥ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዎ​ች​ንም፥ ቆቦ​ች​ንም ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።


በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል በብ​ል​ሃት የተ​ሠ​ሩ​ትን ልብ​ሶች፥ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን የካ​ህ​ኑን የአ​ሮ​ንን ልብ​ሶች፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብ​ሶች አመጡ።


ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ሙሴም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤


ሙሴም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።


ሙሴም ለቅ​ድ​ስና የሚ​ሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ፤


ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰብ​ስ​ባ​ቸው።”


እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች