Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከቍ​ር​ባ​ኑም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድርሻ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ያነ​ሣል። እር​ሱም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደም ለሚ​ረ​ጨው ካህን ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከእያንዳንዱ የኅብስት ዐይነት አንዱን ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ያም መባ የእንስሳውን ደም ወስዶ በመሠዊያው ጐን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለረጨው ካህን ድርሻ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከቍርባኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን እንዲሆን ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:14
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”


ከድ​ር​ሻ​ቸው እኩ​ሌታ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።


እስ​ራ​ኤል ዘሥ​ጋን ተመ​ል​ከቱ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ይበ​ላሉ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ጋር አንድ ይሆኑ አል​ነ​በ​ረ​ምን?


ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች