ዘሌዋውያን 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከእያንዳንዱ የኅብስት ዐይነት አንዱን ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ያም መባ የእንስሳውን ደም ወስዶ በመሠዊያው ጐን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለረጨው ካህን ድርሻ ይሁን፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ከቍርባኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ድርሻ ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ከቍርባኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን እንዲሆን ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |