Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ኀጢአት ቢሠራ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ኃጢአት በአንዱ ቢሠራ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም በማለት በሐሰት ቢምል፥ ሰዎች ከሚፈጽሙአቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 6:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የጠ​ላ​ት​ህን በሬ ወይም አህ​ያ​ውን ጠፍቶ ብታ​ገ​ኘው ፈጽሞ መል​ስ​ለት።


ኀፍ​ረተ ሥጋ​ቸ​ው​ንም ይከ​ድ​ኑ​በት ዘንድ የተ​ልባ እግር ሱሪ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከወ​ገ​ባ​ቸ​ውም እስከ ጭና​ቸው ይደ​ር​ሳል፤


ልጄ ሆይ፥ ነገሬን ፍራ፥ ተቀበለው፥ ንስሓም ግባ፤ ይህንም በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ተናግሬ ፈጸምሁ።


እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።”


ብት​ገ​ድ​ሉም፥ ብታ​መ​ነ​ዝ​ሩም፥ ብት​ሰ​ር​ቁም፥ በሐ​ሰ​ትም ብት​ምሉ፥ ለበ​አ​ልም ብታ​ጥኑ፥ የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ ክፉ ያገ​ኛ​ች​ኋል።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


የሆድ ዕቃ​ው​ንም ከላ​ባ​ዎች ጋር ለይቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል በአ​መዱ ስፍራ ይጥ​ለ​ዋል፤


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የተ​ልባ እግር ቀሚስ ይል​በስ፤ የተ​ልባ እግ​ርም ሱሪ በገ​ላው ላይ ይሁን፤ የተ​ልባ እግር መታ​ጠ​ቂያ ይታ​ጠቅ፤ የተ​ልባ እግር አክ​ሊ​ልም በራሱ ላይ ያድ​ርግ፤ እነ​ዚህ የተ​ቀ​ደሱ ልብ​ሶች ናቸው፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ታጥቦ ይል​በ​ሳ​ቸው።


በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች