Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ኃጢአት በአንዱ ቢሠራ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ቢል ወይም በሐሰት ቢምል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን እንዲህ ያለውን ማንኛውንም ኀጢአት ቢሠራ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወይም የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም በማለት በሐሰት ቢምል፥ ሰዎች ከሚፈጽሙአቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወይም የጠ​ፋ​ውን ነገር ቢያ​ገኝ፥ ስለ​ዚ​ህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢ​አ​ትን ለመ​ሥ​ራት ከሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ በአ​ን​ዲቱ በሐ​ሰት ቢምል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ ቢበድል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 6:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


የጠላትህን በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው ለእርሱ መልስለት።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”


ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤


እነርሱም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ቢሉም እንኳ የሚምሉት በሐሰት ነው።


እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ “ጌታስ ማን ነው?” እንዳልል፥ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ የአምላኬንም ስም እንዳላረክስ።


በባልንጀራህ ላይ በከንቱ ምስክር አትሁን፥ በከንፈርህም አታባብለው።


ኀፍረተ ሥጋቸውን እንዲሸፍኑበት ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ የበፍታ ሱሪ ታደርግላቸዋለህ፤


የሆድ ዕቃውንም ከላባዎቹ ጋር ለይቶ በመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ባለው በአመዱ ስፍራ ይጥለዋል፤


የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።


ወደ ውጭው አደባባይ ወደ ሕዝቡ በሚወጡበት ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፥ በተቀደሰው ቤት ውስጥ ያኑሩት፥ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላ ልብስ ይልበሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች