ዮናስ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ዮናስም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ የመጀመሪያውን ቀን ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ዐወጀ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ዮናስ ወደ ከተማይቱ መግባት ጀመረ፥ የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንደ ገባ “አሁንም ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ጮኸ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ዮናስ ወደ ከተማይቱ ገብቶ ጒዞውን ጀመረ፤ የአንድ ቀን መንገድም እንደ ሄደ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትደመሰሳለች!” ብሎ ዐወጀ። ምዕራፉን ተመልከት |