Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 4:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሳም​ራ​ው​ያ​ንም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ኖር ማለ​ዱት፤ ሁለት ቀንም ያህል በዚያ ተቀ​መጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ስለዚህ፣ ሳምራውያኑ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ዐብሯቸው እንዲቈይ አጥብቀው ለመኑት፤ እዚያም ሁለት ቀን ቈየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ለመኑት፤ በዚያም ለሁለት ቀን ያህል ቆየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ስለዚህ የሰማርያ አገር ሰዎች ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ለመኑት፤ እርሱም ሁለት ቀን እዚያ ቈየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ለመኑት፤ በዚያም ሁለት ቀን ያህል ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 4:40
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


ምክሬን ያዝ፥ አትተውም፤ ለራስህ ጠብቃት፥ እርሷ ሕይወትህ ናትና።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ያን​ጊዜ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን አገ​ኘ​ሁት፥ ያዝ​ሁ​ትም፤ ወደ እና​ቴም ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ እስ​ካ​ገ​ባው ድረስ አል​ተ​ው​ሁ​ትም።


ጌታ ሆይ! አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ነህ፤ በመ​ከ​ራም ጊዜ ታድ​ነ​ዋ​ለህ፤ በም​ድር እንደ እን​ግዳ፥ ወደ ማደ​ሪ​ያም ዘወር እን​ደ​ሚል መን​ገ​ደኛ ስለ ምን ትሆ​ና​ለህ?


ማር​ያም የም​ት​ባል እኅ​ትም ነበ​ረ​ቻት፤ እር​ስ​ዋም ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጣ ትም​ህ​ር​ቱን ትሰማ ነበር።


እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ።


ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ ነገ​ረኝ” ብላ የመ​ሰ​ከ​ረ​ችው ሴት ስለ ነገ​ረ​ቻ​ቸ​ውም ከዚ​ያች ከሰ​ማ​ርያ ከተማ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።


ስለ ቃሉም እጅግ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።


ከሁ​ለት ቀንም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


በዚ​ያ​ችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች