Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ በዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ስለ ማን​ጻት ክር​ክር ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በአንዳንድ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መካከል ስለ መንጻት ሥርዐት ክርክር ተነሣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከልም ስለ ማንጻት ሥርዓት ክርክር ተነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በዚያን ጊዜ በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ መንጻት ሥርዓት ክርክር ተነሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 3:25
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፤ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።”


በዚ​ያም እንደ አይ​ሁድ ልማድ የሚ​ያ​ነ​ጹ​ባ​ቸው ስድ​ስት የድ​ን​ጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁለት ወይም ሦስት እን​ስራ ይይዙ ነበር።


ጥም​ቀ​ትን፥ በአ​ን​ብ​ሮተ እድ መሾ​ምን፥ የሙ​ታ​ንን ትን​ሣ​ኤና የዘ​ለ​ዓ​ለም ፍር​ድን ለመ​ማር ነው።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


በሰ​ማይ ባለው አም​ሳል የተ​ሠ​ራው ይህ ሥራ፥ በዚህ ደም የሚ​ነጻ ከሆነ፥ ይህ ሰማ​ያዊ መሥ​ዋ​ዕ​ትስ ከዚህ ይበ​ል​ጣል።


ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች