Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ፋሲካ ከሚ​ው​ል​በት ከስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው አል​ዓ​ዛር ወደ ነበ​ረ​በት ወደ ቢታ​ንያ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የፋሲካ በዓል ስድስት ቀን ሲቀረው፣ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደሚኖርበት፣ ወደ ቢታንያ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀን ሲቀረው፥ ኢየሱስ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ ቢታንያ ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር የሚኖርባት መንደር ነች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 12:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ፤ በዚያም አደረ።


ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።


እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።


እነሆ፥ ከዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም አን​ዲት ኀጢ​አ​ተኛ ሴት በፈ​ሪ​ሳ​ዊው ቤት በማ​ዕድ እን​ደ​ተ​ቀ​መጠ ዐውቃ ሽቱ የሞ​ላ​በት የአ​ል​ባ​ስ​ጥ​ሮስ ቢል​ቃጥ ገዝታ መጣች።


የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር።


ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ።


ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።


የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲካ በዓል ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከበ​ዓሉ አስ​ቀ​ድሞ ራሳ​ቸ​ውን ያነጹ ዘንድ ከየ​ሀ​ገሩ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተው ነበር።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ለበ​ዓል መጥ​ተው የነ​በሩ ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ደ​ሚ​መጣ በሰሙ ጊዜ፥


ከጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ይሰ​ግዱ ዘንድ ለበ​ዓል የወጡ ነበሩ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች