Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ያለ​በ​ትን የሚ​ያ​ውቅ ቢኖር ይይ​ዙት ዘንድ እን​ዲ​ያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው አዘዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን ይይዙት ዘንድ የት እንዳለ የሚያውቅ ሰው እንዲጠቍም ትእዛዝ ሰጥተው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዝዘው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 ደግሞም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን መያዝ እንዲችሉ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲጠቊማቸው ሰውን ሁሉ አዘው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቀው ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዘው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:57
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳግ​መ​ኛም ሊይ​ዙት ፈለጉ፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም አመ​ለጠ።


ወላ​ጆቹ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክር​ስ​ቶስ ነው ብሎ በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ቢኖር ከም​ኵ​ራብ ይውጣ” ብለው አይ​ሁድ ተስ​ማ​ም​ተው ነበ​ርና።


ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም።


ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ሄደው የከ​ሰ​ሱት ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች