ኢዩኤል 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ጊደሮች ከምሳጋቸው ጠፉ፤ ጎተራዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐውድማዎቹም ፈራረሱ፤ እህሉ ደርቆአልና። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣ በስብሶ ቀርቷል፤ ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤ እህሉ ደርቋልና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ዘሩ በምድር ውስጥ ተበላሸ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የተዘራው እህል ሁሉ በዐፈር ውስጥ በስብሶ ቀርቶአል፤ እህል በመታጣቱ የእህል ማከማቻዎች ሁሉ ባዶ ሆነዋል፤ ጐተራዎችም ፈራርሰዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ዘሩ በምድር ውስጥ በሰበሰ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል። ምዕራፉን ተመልከት |