Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 48:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፤ አልቅሱ ጩኹም፤ ሞዓብ እንደ ጠፋ በአርኖን አጠገብ አውጁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሞአብ ፈራርሳ በዕፍረት ስለ ወደቀች ዋይ ዋይ ብላችሁ አልቅሱላት፤ ባድማ መሆንዋንም በአርኖን ወንዝ አጠገብ ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፥ አልቅሱ ጩኹም፥ ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ አውሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 48:20
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ።


ጫጩ​ቶ​ች​ዋን አሳ​ድጋ እንደ ተወች ወፍ ሆና​ለ​ችና፤ የሞ​ዓብ ሴት ልጅም እንደ ሰባ የበግ ጠቦት ሆነች።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


እስ​ራ​ኤ​ልም በቃ​ዴስ ተቀ​መጠ። በም​ድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንና የሞ​ዓ​ብ​ንም ምድር ዞሩ፤ ከሞ​ዓብ ምድ​ርም በም​ሥ​ራቅ በኩል መጡ፤ በአ​ር​ኖ​ንም ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖ​ንም የሞ​ዓብ ድን​በር ነበ​ረና ወደ ሞዓብ ድን​በር አል​ገ​ቡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች