Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ቀር​ሜ​ሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተ​ሞ​ችም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ነሣ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣ​ውም የተ​ነሣ ፈጽ​መው ጠፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ፍሬያማው ምድር በረሓ ሆነ፤ ከተሞቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከብርቱ ቍጣው የተነሣ ፈራረሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማው እርሻ ምድረ በዳ ሆኖ፥ ከተሞችም ሁሉ ከጌታ ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ለምለሚቱ ምድር ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ከእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ የተነሣ፥ ከተሞችዋ ሁሉ ፈራርሰዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን? እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?


ስን​ዴን ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ እሾ​ህ​ንም ታጭ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ዕጣ​ች​ሁም ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ በአ​ዝ​መ​ራ​ችሁ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ።


በሚ​ኖ​ሩ​ባት ሰዎች ክፋት ምድ​ሪቱ የም​ታ​ለ​ቅ​ሰ​ውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚ​ደ​ር​ቀው እስከ መቼ ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጻ​ሜ​ያ​ች​ንን አያ​ይም ብለ​ዋ​ልና እን​ስ​ሶ​ችና ወፎ​ችም ጠፍ​ተ​ዋል።


ይህ​ችም ምድር ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም አሕ​ዛ​ብና ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገ​ዛሉ።


ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።


በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ።


ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤ የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ።


ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች