Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሚ​ሸ​ሹ​ትን የም​መ​ለ​ከት፥ የመ​ለ​ከ​ቱ​ንስ ድምፅ የም​ሰማ እስከ መቼ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እስከ መቼ የጦርነት ዐርማ እመለከታለሁ? እስከ መቼስ የመለከት ድምፅ እሰማለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሰልፍ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ፥ የጦርነት ድምፅ ሲያስገመግም፥ የጥሩምባም ድምፅ ሲያስተጋባ የምሰማው እስከ መቼ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:21
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


ዓመ​ቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ከእ​ርሱ ጋር አስ​ወ​ሰደ፤ የአ​ባ​ቱን የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ወን​ድም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ።


ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


ንጉ​ሡም ወደ ግብፅ ወሰ​ደው፤ በሀ​ገ​ሩም ላይ መቶ መክ​ሊት ብርና አንድ መክ​ሊት ወርቅ ግብር ጣለ​በት።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።


የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


እና​ን​ተም፦ አይ​ደ​ለም፤ ሰልፍ ወደ​ማ​ና​ይ​ባት፥ የመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ወደ​ማ​ን​ሰ​ማ​ባት፥ እን​ጀ​ራ​ንም ወደ​ማ​ን​ራ​ብ​ባት ወደ ግብፅ ምድር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያም እን​ቀ​መ​ጣ​ለን ብትሉ፥


እና​ንተ የብ​ን​ያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላ​ቅም ጥፋት ከመ​ስዕ ይጐ​በ​ኛ​ልና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ለመ​ሸሽ ጽኑ፤ በቴ​ቁሔ መለ​ከ​ቱን ንፉ፤ በቤ​ት​ካ​ሪም ላይ ምል​ክ​ትን አንሡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች