ኤርምያስ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፥ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም። ምዕራፉን ተመልከት |