Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 39:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የአ​ዛ​ዞች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም ላከ፤ ናቡ​ሻ​ዝ​ባ​ንም፥ ራፋ​ስ​ቂ​ስም፥ ኔር​ጋል ሴራ​አ​ጼ​ርም፥ ራብ​ማ​ግም፥ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ላኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቡሸዝባን፣ ከፍተኛ ሹሙ ኤርጌል ሳራስር እንዲሁም ሌሎች የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን፥ የራፋስቂሱ ናቡሽዝባንም የራብማጉ ኤርጌል ሳራስርም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህም ናቡዛርዳን፥ ናቡሻዝባንና ኔርጋልሻሬጼር ተብለው ከሚጠሩትና ከሌሎችም የባቢሎን ባለ ሥልጣኖች ጋር ሆኖ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፥ ናቡሽዝባንም ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ላኩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 39:13
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤር​ም​ያ​ስም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተያ​ዘ​ች​በት ቀን ድረስ በግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


“ውሰ​ደ​ውና በመ​ል​ካም ተመ​ል​ከ​ተው፤ የሚ​ል​ህ​ንም ነገር አድ​ር​ግ​ለት እንጂ ክፉን ነገር አታ​ድ​ር​ግ​በት።”


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ከግ​ዞት ቤቱ አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት፤ ወደ ቤቱም ይወ​ስ​ደው ዘንድ ለሳ​ፋን ልጅ ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ሰጡት፤ እን​ዲ​ህም በሕ​ዝብ መካ​ከል ተቀ​መጠ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ፥ ማር​ጋ​ና​ሳር፥ ሳማ​ጎት፥ ናቡ​ሳ​ኮር፥ ናቡ​ሰ​ሪስ፥ ናግ​ራ​ጎ​ስ​ና​ሴር፥ ረብ​ማግ፥ ኔር​ጋል ሴሪ​አ​ጼር፥ ከቀ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ጋር ገብ​ተው በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው በር ውስጥ ተቀ​መጡ።


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች