Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 38:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ በመ​ጣ​ላ​ቸው በእ​ርሱ ላይ በአ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ውስጥ እን​ጀራ ስለ​ሌለ በዚያ በራብ ይሞ​ታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ በኤርምያስ ላይ ባደረጉት ነገር ሁሉ ክፋትን አድርገዋል፤ ከከተማዪቱም እንጀራ በጠፋ ጊዜ በራብ እንዲሞት ጕድጓድ ውስጥ ጥለውታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጉድጓድ ውስጥ ጥለው ባደረጉበት ነገር ሁሉ ክፉ ነገርን ፈጽመዋል፤ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለ ሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው በእርሱ ላይ በማድረጋቸው ሁሉ ክፉ አድርገዋል፥ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 38:9
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከብዙ ሕዝብ የተ​ነሣ በፊ​ታ​ቸው ለመ​ና​ገር አፍሬ እንደ ሆነ፥ ድሃ​ውም ከደጄ ባዶ​ውን ወጥቶ እንደ ሆነ፥


የወ​ን​ዶ​ችና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሥጋ አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ውን የሚ​ሹት በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ጭን​ቀ​ትና መከ​በብ የባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሥጋ ይበ​ላሉ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።


ንጉ​ሡም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “ከአ​ንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ሳይ​ሞት ከጕ​ድ​ጓድ አው​ጣው” ብሎ አዘ​ዘው።


ንጉ​ሡም በብ​ን​ያም በር ተቀ​ምጦ ነበር። አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከን​ጉሡ ቤት ወጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥


በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ።


ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


ጠላ​ቶች ሕይ​ወ​ቴን በጕ​ድ​ጓድ አጠፉ፤ በላ​ዬም ድን​ጋይ ገጠሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች