Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ነገር ግን ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሥራ፥ በጎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ላሞ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ እፍ​ረት በል​ቶ​ባ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከለጋ ዕድሜያችን ጀምሮ፣ የአባቶቻችንን የድካም ፍሬዎች፣ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ነውረኛ ጣዖቶች በሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችን ድካም፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ አሳፋሪ ነገር በልቶባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ነገር ግን አሳፋሪ ለሆኑ ጣዖቶች መስገዳችን፥ የበግና የከብት መንጋዎቻችንን ሁሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ሁሉ፥ ከጥንት ጀምሮ የቀድሞ አባቶቻችን ደክመው ያፈሩልንን ሀብት ሁሉ እንድናጣ አድርጎናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችን ድካም፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 3:24
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁዳ ሆይ! አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መን​ገ​ዶች ቍጥር ለነ​ው​ረኛ ነገር ለበ​ዓል ታጥ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን አድ​ር​ጋ​ች​ኋል።


በጐ​ሰ​ቈ​ልሽ ጊዜ ተና​ገ​ር​ሁሽ፤ አን​ቺም፦ አል​ሰ​ማም አልሽ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ቃሌን አለ​መ​ስ​ማ​ትሽ መን​ገ​ድሽ ነው።


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


የፈ​ረ​ሶ​ቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠ​ራ​ዊቱ ፈረ​ሶች ሩጫ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ምድር በመ​ላዋ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ መጥ​ተ​ውም ምድ​ሪ​ቱ​ንና በእ​ር​ስ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ት​ንም በሉ።


ፈጥ​ነ​ውም ሙሾ ያሙ​ሹ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም እን​ባን ያፍ​ስሱ፤ ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ሽፋ​ሽ​ፍ​ቶች ውኃ ይፍ​ለቅ።


የሰ​ጠ​ሁ​ሽ​ንም እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ያበ​ላ​ሁ​ሽ​ንም ዱቄ​ትና ዘይ​ቱን፥ ማሩ​ንም ጣፋጭ ሽታ አድ​ር​ገሽ በፊ​ታ​ቸው አኖ​ርሽ፤ እን​ዲ​ህም ሆኖ​አል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለእ​ኔም የወ​ለ​ድ​ሻ​ቸ​ውን ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ወስ​ደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋ​ሽ​ላ​ቸው፤ ገደ​ል​ሻ​ቸ​ውም።


ታላ​ቆ​ቹ​ንና ታና​ሾ​ቹን እኅ​ቶ​ች​ሽ​ንም በተ​ቀ​በ​ልሽ ጊዜ መን​ገ​ድ​ሽን ታስ​ቢ​ያ​ለሽ፤ ታፍ​ሪ​ማ​ለሽ፤ ለአ​ን​ቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ቃል ኪዳ​ንሽ ግን አይ​ደ​ለም።


ታስቢ ዘንድ፥ ታፍ​ሪም ዘንድ፥ ደግ​ሞም ስላ​ደ​ረ​ግ​ሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባል​ሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍ​ረ​ትሽ አፍ​ሽን ትከ​ፍቺ ዘንድ አይ​ቻ​ል​ሽም፤” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል።


እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች።


እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች