ኤርምያስ 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 “ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችን ድካም፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ አሳፋሪ ነገር በልቶባቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ከለጋ ዕድሜያችን ጀምሮ፣ የአባቶቻችንን የድካም ፍሬዎች፣ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ነውረኛ ጣዖቶች በሏቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ነገር ግን አሳፋሪ ለሆኑ ጣዖቶች መስገዳችን፥ የበግና የከብት መንጋዎቻችንን ሁሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ሁሉ፥ ከጥንት ጀምሮ የቀድሞ አባቶቻችን ደክመው ያፈሩልንን ሀብት ሁሉ እንድናጣ አድርጎናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችንን ሥራ፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችን ድካም፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል። ምዕራፉን ተመልከት |