Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 27:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ር​ሱን አት​ስሙ፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ፤ ይህ​ችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆ​ና​ለች?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ባለመታዘዛችሁስ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱን አትስሙ፤ ለባቢሎን ንጉሥ አገልግሉ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ለምን ባድማ ትሆናለች?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ብትገዙለት በሕይወት ትኖራላችሁ፤ ይህችስ ከተማ ስለምን የፍርስራሽ ክምር ሆና ትቀራለች?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እነርሱም አትስሙ፥ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 27:17
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤር​ም​ያ​ስም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ብት​ወጣ፥ ነፍ​ስህ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት አት​ቃ​ጠ​ልም፤ አን​ተም፥ ቤት​ህም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ሁሉ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ያወ​ጣሉ፤ አን​ተም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትያ​ዛ​ለህ እንጂ ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት ትቃ​ጠ​ላ​ለች።”


ከም​ት​ፈ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት አት​ፍሩ፤ አድ​ና​ችሁ ዘንድ፥ ከእ​ጁም አስ​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍሩ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች