ኤርምያስ 27:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እነርሱን አትስሙ፤ ለባቢሎን ንጉሥ አገልግሉ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ለምን ባድማ ትሆናለች? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ባለመታዘዛችሁስ ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ስለዚህ እነርሱን መስማት ትታችሁ ለባቢሎን ንጉሥ ብትገዙለት በሕይወት ትኖራላችሁ፤ ይህችስ ከተማ ስለምን የፍርስራሽ ክምር ሆና ትቀራለች? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እነርሱን አትስሙ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ፤ በሕይወትም ኑሩ፤ ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እነርሱም አትስሙ፥ ለባቢሎን ንጉሥ ተገዙ በሕይወትም ኑሩ። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች? ምዕራፉን ተመልከት |