Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም ለአ​ለ​ቆ​ቹና ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ እንደ ሰማ​ችሁ በዚች ከተማ ላይ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይህ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው” ብለው ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለባለሥልጣኖቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “በጆሯችሁ እንደ ሰማችሁት ይህ ሰው በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ስለ ተናገረ ሞት ይገባዋል” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯልና ይህ ሰው ሞት ይገባዋል” ብለው ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው ብለው ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 26:11
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ግን አቤቱ! ይገ​ድ​ሉኝ ዘንድ በላዬ የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር አት​በል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከፊ​ትህ አት​ደ​ም​ስስ፤ በፊ​ት​ህም ይው​ደቁ፤ በቍ​ጣህ ጊዜ እን​ዲሁ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።”


አለ​ቆ​ቹና ሕዝ​ቡም ሁሉ ለካ​ህ​ና​ትና ለነ​ቢ​ያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተና​ግ​ሮ​ና​ልና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም” አሉ።


አለ​ቆ​ቹም ንጉ​ሡን፥ “ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ቃል ሲነ​ግ​ራ​ቸው በዚ​ያች ከተማ የቀ​ሩ​ትን የሰ​ል​ፈ​ኞ​ቹን እጅ፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ እጅ ያደ​ክ​ማ​ልና ይህ ሰው ይገ​ደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋ​ትን እንጂ ሰላ​ምን አይ​መ​ኝ​ለ​ት​ምና” አሉት።


እነርሱም “ሞት ይገባዋል!” ብለው መለሱ።


እነ​ር​ሱም፥ “ክፉ የሠራ ባይ​ሆ​ንስ ወደ አንተ አሳ​ል​ፈን ባል​ሰ​ጠ​ነው ነበር” ብለው መለ​ሱ​ለት።


አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ሊሞት ይገ​ባል፤ ራሱን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አድ​ር​ጎ​አ​ልና” አሉት።


ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።


ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።


የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ኢዮ​አ​ስን፥ “የበ​ዓ​ልን መሠ​ዊያ አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸድ ቈር​ጦ​አ​ልና ይገ​ደል ዘንድ ልጅ​ህን አምጣ” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች