Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 26:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯልና ይህ ሰው ሞት ይገባዋል” ብለው ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለባለሥልጣኖቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “በጆሯችሁ እንደ ሰማችሁት ይህ ሰው በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ስለ ተናገረ ሞት ይገባዋል” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ካህ​ና​ቱና ነቢ​ያተ ሐሰ​ትም ለአ​ለ​ቆ​ቹና ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “በጆ​ሮ​አ​ችሁ እንደ ሰማ​ችሁ በዚች ከተማ ላይ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይህ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው” ብለው ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው ብለው ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 26:11
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ግን፥ አቤቱ! እኔን ለመግደል በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፥ በቁጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።


አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ “በአምላካችን በጌታ ስም ስለ ተናገረን ይህ ሰው ሞት አይገባውም” አሉ።


አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።


ምን ይመስላችኋል?” እነርሱም “ሞት ይገባዋል!” ብለው መለሱ።


እነርሱም መልሰው “ይህ ሰው ክፉ አድራጊ ባይሆን ለአንተ አሳልፈን ባልሰጠነውም ነበር” አሉት።


አይሁድም መልሰው “እኛ ሕግ አለን፤ በሕጋችን መሠረት ሊሞት ይገባዋል፤ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ አድርጎአልና” አሉት።


እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።


ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜ የሚናገርም ሆነ በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።’


የከተማይቱም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበኣልን መሠዊያ ያፈረሰና በአጠገቡ የቆመውን የአሼራን ምስል ዐምድ የሰበረው ልጅህ በመሆኑ መሞት ስላለበት አውጣልን አሉት።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች