Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 11:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እኔም ለመ​ታ​ረድ እን​ደ​ሚ​ነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ን​ጀ​ራው ዕን​ጨት እን​ጨ​ምር ስሙም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ እን​ዳ​ይ​ታ​ሰብ ከሕ​ያ​ዋን ምድር እና​ጥ​ፋው ብለው ክፉ ምክ​ርን እን​ዳ​ሰ​ቡ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣ “ዛፉን ከፍሬው ጋራ እንቍረጥ፤ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ” ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ወደ ዕርድ እንደሚሄድ የበግ ጠቦት ሆኜ ነበር፤ እነርሱ “ስሙ ዳግመኛ እንዳይታወስ ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፤ ከሕያዋያን ዓለም እናስወግደው” ብለው በእኔ ላይ ማደማቸውን አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፥ እነርሱም፦ ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 11:19
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሟች ሰው መን​ገ​ድ​ዋን አያ​ው​ቅም፤ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ አት​ገ​ኝም።


በሰ​ማ​ይና በም​ድር የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን የሚ​ያይ፤


የቀ​ድ​ሞ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፥ ሥራ​ህ​ንም ሁሉ አነ​በ​ብሁ፤ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ አነ​ብ​ባ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።


በቤ​ትህ የሚ​ኖሩ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያመ​ስ​ግ​ኑ​ሃል።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥


እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥


በዐ​መ​ፃ​ቸው ነገር ድሃ​ውን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ፥ የድ​ሆ​ች​ንም ፍርድ ይገ​ለ​ብጡ ዘንድ የክ​ፉ​ዎች ሕሊና ዐመ​ፅን ትመ​ክ​ራ​ለች።


ደግ​ሞም፦ በሕ​ያ​ዋን ምድር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም መዳን በም​ድር ላይ አላ​ይም፤ ከዘ​መ​ዶ​ችም ሰውን አላ​ይም።


ከአ​ንተ ጋር ይዋ​ጋሉ፤ ነገር ግን አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ድል አይ​ነ​ሡ​ህም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ይና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ በፈ​ጸመ ጊዜ ካህ​ና​ትና ነቢ​ያተ ሐሰት፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞ​ታ​ለህ” ብለው ያዙት።


በቀ​ላ​ቸ​ውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ አየህ።


“ኤላ​ምም በዚያ አለች፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ ሳይ​ገ​ረ​ዙም ወደ ታች​ኛው ምድር ወር​ደ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ተ​ዋል።


ኤፍ​ሬም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ጉበኛ ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመ​ን​ገዱ ሁሉ ላይ ክፉ ወጥ​መድ ሆነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ርኵ​ሰ​ትን አደ​ረጉ።


ከጋድ የራ​ጉ​ኤል ልጅ ኤል​ሳፍ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች