ሆሴዕ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እስኪጠፉ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ እሄዳለሁ፤ ወደ ስፍራዬም እመለሳለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ ፊቴን ይሻሉ፤ በመከራቸውም አጥብቀው ይፈልጉኛል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በደላቸውንም ተቀብለው ፊቴን እስኪሹ ድረስ ወደ ስፍራዬ ተመልሼ እሄዳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “መከራ ሲበዛባቸው እኔን ይፈልጋሉ፤ ስለዚህ የሠሩትን በደል ተገንዝበው ወደ እኔ እስከሚመለሱ፥ ድረስ ከእነርሱ እርቃለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ ሄጄ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፥ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ። ምዕራፉን ተመልከት |