Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ሕያው ነፍስ ባለ​ውም ሥጋ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ው​ንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃን አላ​መ​ጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በእኔና በእናንተ፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ፍጥረት መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ውኃም ዳግመኛ ፍጥረትን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የውኃ ሙላት አይመጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ‘ከእንግዲህ ወዲህ የጥፋት ውሃ፤ ሕያዋን ፍጥረቶችን ሁሉ ከቶ አያጠፋም’ ብዬ ከእናንተና ከሌሎች ሕያዋን ፍጥረቶች ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፉ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 9:15
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።


ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል።


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ውም ሁሉ ዳግ​መኛ በጥ​ፋት ውኃ አይ​ጠ​ፋም፤ ምድ​ር​ንም ለማ​ጥ​ፋት ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃ አይ​ሆ​ንም።”


በም​ድር ላይ ደመ​ናን በጋ​ረ​ድሁ ጊዜ ቀስቴ በደ​መ​ናው ትታ​ያ​ለች፤


እን​ዲ​ህም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልቡ በፊ​ትህ ለሚ​ሄድ ባሪ​ያህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥


“አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ ታላ​ቅና ኀያል ጽኑ​ዕና የተ​ፈ​ራ​ኸው አም​ላክ ሆይ፥ ከአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእ​ኛና በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ በአ​ለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ በካ​ህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በሕ​ዝ​ብህ ሁሉ ላይ የደ​ረ​ሰው መከራ ሁሉ በፊ​ትህ ጥቂት መስሎ አይ​ታ​ይህ።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለ​ቱን ዕን​ቍ​ዎች በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አሮ​ንም በሁ​ለቱ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ስማ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሸ​ከ​ማል።


ስለ ስምህ ብለህ ተመ​ለ​ስ​ልን፤ የክ​ብ​ር​ህ​ንም ዙፋን አታ​ጥፋ፤ ከእኛ ጋርም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ቃል ኪዳ​ን​ህን አስብ እንጂ አታ​ፍ​ርስ።


ነገር ግን በሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ወራት ከአ​ንቺ ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን ዐስ​ባ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ቃል ኪዳን አጸ​ና​ል​ሻ​ለሁ።


ቸር​ነ​ቱን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ርግ ዘንድ፥ ቅዱስ ኪዳ​ኑ​ንም ያስብ ዘንድ።


አን​ተም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ትም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምሕ​ረ​ቱን እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ የሚ​ጠ​ብቅ የታ​መነ አም​ላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች