Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ቀስ​ቴም በደ​መና ትሆ​ና​ለች፤ በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል፥ በም​ድር ላይ በሚ​ኖር ሥጋ ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ለማ​ሰብ አያ​ታ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔርና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን ዐስባለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ቀስቲቱም በደመና ስትሆን፥ አያታለሁም በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ፍጥረት ሁሉ መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ቀስቲቱም በደመነ ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባከው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 9:16
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ል​መ​ለስ፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን እገ​ባ​ለሁ፤ ከእ​ኔም ዘንድ ፈቀቅ እን​ዳ​ይሉ መፈ​ራ​ቴን በል​ባ​ቸው ውስጥ አኖ​ራ​ለሁ።


በውኑ ቤቴ በኀ​ያሉ ዘንድ እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ምን? ከእ​ኔም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጀና የተ​ጠ​በቀ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን አድ​ር​ጎ​አል፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ፈቃ​ዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመ​ፀ​ኛም አይ​በ​ቅ​ል​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስ​ትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ይስ​ሐቅ ብለህ ትጠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ በኋላ ለዘሩ አም​ላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳ​ኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ከእ​ርሱ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።


በቤ​ት​ህም የተ​ወ​ለደ፥ በብ​ርም የተ​ገዛ ፈጽሞ ይገ​ረዝ። ቃል ኪዳ​ኔም በሥ​ጋ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ይሆ​ናል።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ “በእ​ኔና በም​ድር ላይ በሚ​ኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካ​ከል ያጸ​ና​ሁት የቃል ኪዳን ምል​ክት ይህ ነው” አለው።


እነ​ር​ሱ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታዬ ዙሪያ ያሉ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዝና​ቡ​ንም በጊ​ዜው አወ​ር​ዳ​ለሁ፤ የበ​ረ​ከ​ትም ዝናብ ይሆ​ናል።


የሰ​ላ​ምም ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አኖ​ራ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች