Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 43:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ለእ​ር​ሱም ለብ​ቻው አቀ​ረቡ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ለብ​ቻ​ቸው፤ ከእ​ርሱ ጋር ለሚ​በ​ሉት ለግ​ብፅ ሰዎ​ችም ለብ​ቻ​ቸው፤ የግ​ብፅ ሰዎች ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ጋር መብ​ላት አይ​ች​ሉ​ምና፥ ይህ ለግ​ብፅ ሰዎች እንደ መር​ከስ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከርሱ ጋራ ለሚበሉት ግብጻውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋራ ዐብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ስለ ነበር ለዮሴፍ ብቻውን አንድ ገበታ፥ ለወንድማማቾቹ ሌላ ገበታ፥ እዚያ ይመገቡ ለነበሩ ግብጻውያንም ሌላ ገበታ ተዘጋጀ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 43:32
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።


ዮሴ​ፍም ብን​ያ​ምን ከእ​ነ​ርሱ ጋር በአ​የው ጊዜ የቤ​ቱን አዛዥ እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ወደ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እር​ድም እረድ፤ አዘ​ጋ​ጅም፤ እነ​ዚያ ሰዎች በእ​ኩለ ቀን ከእኔ ጋር ይበ​ላ​ሉና።”


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።


ሙሴም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እን​ሠ​ዋ​ለ​ንና እን​ዲሁ ይሆን ዘንድ አይ​ቻ​ልም፤ እነሆ፥ ግብ​ፃ​ው​ያን እርም የሚ​ሉ​ትን እኛ በፊ​ታ​ቸው ብን​ሠዋ በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች