ዘፍጥረት 43:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከርሱ ጋራ ለሚበሉት ግብጻውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋራ ዐብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ስለ ነበር ለዮሴፍ ብቻውን አንድ ገበታ፥ ለወንድማማቾቹ ሌላ ገበታ፥ እዚያ ይመገቡ ለነበሩ ግብጻውያንም ሌላ ገበታ ተዘጋጀ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ፤ ለእነርሱም ለብቻቸው፤ ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው፤ የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይችሉምና፥ ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና። ምዕራፉን ተመልከት |