Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፣ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብጻውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ራቡ በመላው የግብጽ ምድር መስፋፋት ሲጀምር፥ ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፈርዖንም ግብፃውያኑን፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ራብ በመላው ግብጽ ምድር እየተስፋፋ በሄደ ጊዜ፥ ሕዝቡ ወደ ፈርዖን ሄዶ “ምግብ ስጠን!” ብሎ ጮኸ። ፈርዖንም “ወደ ዮሴፍ ሂዱና እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” ብሎ አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:55
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።


ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


እና​ቱም ለአ​ሳ​ላ​ፊ​ዎቹ፥ “የሚ​ላ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ርጉ” አለ​ቻ​ቸው።


ፈጣ​ሪዬ እንደ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ መጠን፥ በክ​ብር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋል።


ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች