Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፣ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 ራቡ በመላው ግብጽ እየተስፋፋና እየበረታ ስለ ሄደ፥ ዮሴፍ ጐተራዎቹ ሁሉ ተከፍተው እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥላቸው አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:56
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት።


እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።


በም​ድር በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ላይ እንደ ተዘ​ረ​ጋች ወጥ​መድ ትደ​ር​ሳ​ለ​ችና።


እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።


ከሰባ ዓመ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጢሮ​ስን በይ​ቅ​ርታ ይጐ​በ​ኛ​ታል፤ ወደ ጥን​ቷም ትመ​ለ​ሳ​ለች፤ ደግ​ሞም ለዓ​ለም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መና​ገ​ሻና መና​ገጃ ትሆ​ና​ለች።


ደግ​ሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመ​ጣል፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የነ​በ​ረ​ው​ንም ጥጋብ ሁሉ ይረ​ሱ​ታል፤ ራብም ምድ​ርን ሁሉ ያጠ​ፋል፤


የግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ተራበ፤ ሕዝ​ቡም ስለ እህል ወደ ፈር​ዖን ጮኸ፤ ፈር​ዖ​ንም የግ​ብፅ ሰዎ​ችን ሁሉ፥ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ እርሱ ያላ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።


ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።


የሚ​መ​ጡ​ትን የመ​ል​ካ​ሞ​ቹን ሰባት ዓመ​ታት እህ​ላ​ቸ​ውን ያከ​ማቹ፤ ስን​ዴ​ው​ንም ከፈ​ር​ዖን እጅ በታች ያኑሩ፤ እህ​ሎ​ችም በከ​ተ​ሞች ይጠ​በቁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች