Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 37:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው። ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን እየጠበቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እንድልክህ ና” አለው። እርሱም “እነሆኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና አለው። እርሱም እነሆኝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 37:13
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ጠራና፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ይስ​ሐቅ ፈጽሞ ከአ​ረጀ በኋላ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር። ታላ​ቁን ልጁን ዔሳ​ው​ንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።


ወደ አባ​ቱም አግ​ብቶ፥ “አባቴ ሆይ፥” አለው፦ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ፤ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ።


ያዕ​ቆ​ብም ከሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በተ​መ​ለሰ ጊዜ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰቂ​ሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።


ወን​ድ​ሞ​ቹም በሴ​ኬም የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን በጎች ይጠ​ብቁ ዘንድ ሄዱ።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


የወ​ይኑ ባለ​ቤ​ትም፦ እን​ግ​ዲህ ምን ላድ​ርግ? ምና​ል​ባት እር​ሱን እንኳ አይ​ተው ያፍሩ እንደ ሆነ የም​ወ​ደ​ውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው።


ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙ​ኤል ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ ጠራው። እር​ሱም ተነ​ሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን እንደ ጠራው አስ​ተ​ዋለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች