Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 37:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን እየጠበቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እንድልክህ ና” አለው። እርሱም “እነሆኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው። ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እስራኤልም ዮሴፍን፦ ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና አለው። እርሱም እነሆኝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 37:13
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፥ “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።


ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ።


እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።


ወደ አባቱም ገብቶ፦ “አባቴ ሆይ” አለው እርሱም፦ “እነሆኝ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ።


ያዕቆብም፥ ከፓዳን-ኣሪም በተመለሰ ጊዜ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው፥ ሴኬም ከተማ በሰላም መጣ፥ እናም በከተማይቱ ፊት ለፊት ሰፈረ።


ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


የወይኑ አትክልት ጌታም ‘ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልካለሁ፤ ምናልባት እርሱን አይተው ያፍሩታል፤’ አለ።


ዔሊ ግን ሳሙኤልን፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፥ “እነሆኝ” ሲል መለሰ።


ጌታም ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም በዚህ ጊዜ ሳሙኤልን ይጠራ የነበረው ጌታ መሆኑን ተረዳ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች