Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 31:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 እኔ ወደ አንተ በክ​ፋት ባልፍ ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር፥ ይህ​ችም ሐው​ልት በክፉ ነገር ትከ​ተ​ለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ይህን ክምር ድንጋይ ዐልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት ዐልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፣ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 እኔ ወደ አንተ ይህን ክምር እንዳላልፍ፥ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህን ክምርና ይህን ሐውልት እንዳታልፍ፥ ይህ ክምር እና ይህ ሐውልት ምስክር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 እኔ አንተን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልል እንደማላልፍ፥ አንተም እኔን ለማጥቃት ይህን የድንጋይ ቊልልና ይህን የመታሰቢያ ሐውልት እንደማታልፍ፥ ይህ የድንጋይ ቊልልና ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ምስክሮች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 እኔ ወደ አንተ ይህችን ክምር እንዳላልፍ አንተም ለክፋት ወደ እኔ ይህችን ክምርና ይህችን ሐውልት እንዳታልፋት ይህች ክምር ምስክር ናት ይህችም ሐውልት ምስክር ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 31:52
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላባም፥ “ይህች ያቆ​ም​ኋት የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ዛሬ ምስ​ክር ናት” አለ። ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ።


ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “እነሆ፥ ይህች የድ​ን​ጋይ ክም​ርና ይህ​ችም ሐው​ልት ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


አን​ተም ወደ እኔ ብታ​ልፍ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የና​ኮ​ርም አም​ላክ በእኛ መካ​ከል ይፍ​ረድ።” ያዕ​ቆ​ብም በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ማለ።


ነገር ግን በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ኛም በኋላ በት​ው​ል​ዳ​ች​ንና በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል በሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና በቍ​ር​ባን፥ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆ​ቻ​ችሁ ልጆ​ቻ​ች​ንን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላ​ች​ሁም እን​ዳ​ይሉ ምስ​ክር ይሆ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች